loading
ዳሸን ባንክ ሁለተኛውን ዙር የዳሸን ከፍታ የስራ ፈጠራ ስልጠና ውድድር መርሃ ግብር በድሬዳዋ ከተማ ይፋ አደረገ::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2014 ዳሸን ባንክ ሁለተኛውን ዙር የዳሸን ከፍታ የስራ ፈጠራ ስልጠና ውድድር መርሃ ግብር በድሬዳዋ ከተማ ይፋ አደረገ:: ባንኩ ማኅበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት በርካታ ፕሮጀክቶችን ነድፎ ተግባራዊ ያደረገ ሲሆን በዚህም በርካቶች ተጠቃሚ ሆነዋል ተብሏል፡፡ የባንኩ የማርኬቲንግ ኮምዩኒኬሽን ከፍተኛ ስራ አስኪያጅ ስለሺ ይልማና የዳሸን ባንክ የድሬዳዋ ቀጠና ፅህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ኑሪት መሀመድ በተገኙበት መርሃ ግብር ባንኩ በሚሰራባቸዉ
አካባቢዎች የህብረተሰቡን ችግሮች ነቅሶ በማዉጣት ችግር ፈች ተግባራትን ማከናወኑ ተገልጿል፡፡

ባለፈዉ ዓመት የተጀመረው በስራ ፈጠራ ላይ ያተኮረ ስልጠናና ዉድድር በዚህ ዓመትም ቀጥሎ መርሃግብሩ በስድስት ከተሞች በሃዋሳ፤ ድሬዳዋ፤ አዳማ፤ ደሴ፤ባህር ዳርና አዲስ አበባ እንዲከናወን ታቅዶ ተግባራዊ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡ በድሬዳዋ ከተማም ዛሬ በተጀመረው ሁለተኛው ዙር የስራ ፈጠራ ስልጠና ውድድር በርካታ ወጣቶች በመሳትፍ ላይ እንደሚገኙ የተገለጸ ሲሆን በመርሃግብሩ መሰረት ለወጣቶቹ አርአያ የሚሆንና ይበልጥ ለስራና ፈጠራ ማነሳሳት የሚያስችሉ የተመረጡ ምርትና አገልግሎቶች ይጎበኛሉ ተብሏል፡፡


የሥልጠና ውድድሩ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት የሚሰጥ ሲሆን ባንኩ በዉድድሩ አሸናፊ ለሚሆኑ ስራ ፈጣሪ ተወዳዳሪዎች ዳጎስ ያለ ሽልማት ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡ እንደ ባልደረባችን ዳዊት ዳኜ ዘገባ የዳሸን ከፍታ ፕሮጀክት በአጠቃላይ ስድስት ዋና ዋና ክፍሎች ያሉት ሲሆን ፤እነሱም የሥራ ፈጠራ ስልጠና፤ የጥቃቅን አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች አቅም ግንባታ፤ የከፍተኛ ትምህርት የፋይናንስ ድጋፍ መርሃ-ግብር፣ የፋይናንስ ተደራሽነት መርሃ-ግብር፣ የቢዝነስ ክለብ ምስረታ፣ እና የገበያ ትስስርና የእሴት ሠንሰለት የፋይናንስ ድጋፍ ናቸው።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *