loading
ዳያስፖራው ለሕዳሴው ግድብ ግንባታ 50 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ድጋፍ ማድረጉ ተገለጸ ፡፡

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 22 ፣ 2013 ዳያስፖራው ለሕዳሴው ግድብ ግንባታ 50 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ድጋፍ ማድረጉ ተገለጸ ፡፡ ዳያስፖራው ባለፉት 10 ዓመታት ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ 50 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ድጋፍ ማድረጉን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ አስታወቀ።የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓም መቀመጡ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት እንደሚናገሩት፤ ዳያስፖራው ኢትዮጵያ በራሷ ወጪ ለምትገነባው ግድብ በቦንድ ግዢና በስጦታ እየደገፈነው።የግድቡ መሰረት ድንጋይ በተጣለበት ዓመት ከ13 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዶላር በላይድጋፍ፤ማድረጉንና ይህም እስካሁን ዳያስፖራው ለግድቡ ግንባታ ካደረገው ድጋፍ ከፍተኛው ነው ብለዋል።

ከ2005 እስከ 2009 ይደረግ የነበረው ድጋፍ ጥሩ የሚባል እንደነበረም ያስታውሳሉ።እስከ 2012 ባለው ጊዜ ድጋፉ መቀዛቀዝ እንደታየበትና በሶስት ዓመታት የተደረገው ድጋፍ ከአንድ ሚሊዮን ዶላር በታች ነበር ብለዋል።መንግሥት የግድቡን ግንባታን ለማፋጠን የወሰዳቸው እርምጃዎችና የመጀመሪያው ዙርየውሃ ሙሌት ዳያስፖራው ላይ ከፍተኛ መነቃቃት እንደፈጠረ ተናግረዋል።

በአጠቃላይ ዳያስፖራው ለግድቡ ግንባታ ባለፉት 10 ዓመታት ጊዜ ውስጥ 50 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ድጋፍ በቦንድ ግዢና ስጦታ ማድረጉን ነው ወይዘሮ ሰላማዊት የገለጹት።ባለፈው ዓመት የተካሄደ የመጀመሪያው ዙር የውሃ ሙሌት የፈጠረው መነቃቃት በ2013 በጀት ዓመት ከ3 ነጥብ 1 ሚሊዮን  ዶላር በላይ ድጋፍ ማድረጉን አመልክተዋል።እስካሁን የተደረገው ድጋፍ ባለፈው በጀት ዓመት ከተሰበሰበው ገንዘብ ከ50 በመቶ በላይ ብልጫ እንዳለው ገልጸዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *