loading
ጀግኒት ሀገር አቀፍ የሴቶች የሰላም ኮንፈረንስና ንቅናቄ ፕሮግራም ሊጀመር ነዉ

ጀግኒት ሀገር አቀፍ የሴቶች የሰላም ኮንፈረንስና ንቅናቄ ፕሮግራም ሊጀመር ነዉ

አርትስ 21/02/2011

 “ጀግኒት አለመች፣አቀደች አሳካች” በሚል መሪ ቃል ከሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ሴቶች የሚሳተፉበት ሀገር አቀፍ የሴቶች የሰላም ኮንፈረንስ የፊታችን ጥቅምት 26 ቀንእንደሚካሄድም ተገለጸ።

ይህንኑ ሀገራዊ የህብረተሰብ ንቅናቄ ዝግጅትን አስመልክቶ ዘጠኙ ሴት ሚኒስትሮችና የሁለቱ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤና ምክትል አፈ ጉባኤዎች በተገኙበት ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል።

በመግለጫው ላይ ንግግር ያደረጉት የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር ወይዘሮ ያለም ፀጋይ እንደተናገሩት ኮንፈረንሱ በሀገሪቱ ውስጥ ዘላቂ ሰላም በማረጋገጥ፤ የሴቶችና ህፃናትን የአደጋ ተጋላጭነትበመቀነስ መብትና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ እና የሴቶች ሰላም መከበር ያላቸውን አበርክቶ ለማሳደግ ያለመ ነው ብለዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *