loading
ጂ አይ ዜድ እና ኦሬንጅ የኦሬንጅ በይነ መረብ ማዕከልን በኢትዮጵያ ከፈቱ፡፡

ጂ አይ ዜድ እና ኦሬንጅ የኦሬንጅ በይነ መረብ ማዕከልን በኢትዮጵያ ከፈቱ፡፡ ማዕከሉ በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምሥራቃዊ አፍሪካ ሶስተኛውና ወጣቶችን በበይነ መረብ ቴክኖሎጂ ለማሠልጠንና የተሻለ የሥራ ዕድል እንዲኖራቸው የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከዚህ ባለፈም ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር የዲጂታል ክህሎትን የሚያጎለብትና ለልዩ ልዩ ፈጠራዎች የሚያነሳሳ የኦሬንጅ ዲጂታል ማዕከል ነው ተብሏል፡፡ በማዕከሉ የምረቃ ሥነ ሥርዓት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ ተገኝተዋል።

በ500 ሜትር ስኩዌር ላይ ያረፈው ዲጂታል ማዕከል ስትራቴጂካዊ ፕሮግራሞችን አቅፎ በመያዝ በምሥራቅ አፍሪካ የመጀመሪያው ማዕከል ሲሆን፥ በሀገራት መካከል የሚኖረውን የዕውቀት እና የልምድ ልውውጥ በማጎልበት የወጣቶችን የሥራ ዕድል በቀላል እና በልዩ ልዩ አማራጮች እንደሚያዳብር ታምኖበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የሥራ ፈጠራን በማበረታታት ሀገራዊ የዲጂታል ሥነ ምህዳርን ያስተዋውቃልም ነው የተባለው፡፡ ማእከሉ በቀጣይ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በክልሎች ስራ እንደሚጀምርም ተጠቁሟል::

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *