ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ፈረንሳይ ተጉዘዋል
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ፈረንሳይ ተጉዘዋል
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፈረንሳይ ቆይታቸው ከፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር የሁለቱን ሀገራት የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብር ለማጠናከር በሚቻልበት ጉዳይ ላይይመክራሉ።
የፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ በኢትዮጵያ ተሳትፎውን እንዲያሳድግ እንዲሁም በፈረንሳይ ያለውን ቅርስን የመጠበቅና የመንከባከብ ክህሎት የኢትዮጵያ ቅርሶችን ለመታደግመዋል በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ይወያያሉ።
ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ወደ ፈረንሳይ ያቀኑት ኢማኑኤል ማክሮን ከወራት በፊት ያቀረቡላቸውን ግብዣ ተከትሎ ነው።
ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ ከፓሪስ ቆይታ በኋለ ወደ ጀርመን በርሊን በማቅናት የቡድን 20 አባል ሀገራት በሚያዘጋጁትና በአፍሪካ ጉዳይ ላይ በሚመክረው ኮምፓክትአፍሪካ ጉበኤ ላይ ይሳተፋሉ።
ጠቅላይ ሚንስትሩ በጀርመን ቆይታቸው ከመራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ጋር ተገናኝተው የሁለቱን ሀገራት የልማት ትብብር የበለጠ ለማጠናካር በሚቻልበት ጉዳይ ላይይወየያሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ፍራንክ ፈርት በማምራትም አንድ ሆነን አንነሳ ነገን እንገባ በሚል መርህ በተዘጋጀው የኢትዮጵያውያን መድረክ ላይም ይገኛሉ።
በዚህ መድረክ ከ20ሺ በላይ ከመላው አውሮፓ የተውጣጡ ኢትየጵያውያን ከጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ጋር ይወያያሉ በሀገራቸው ሁለንተናዊ ልማት ላይበሚሳተፉበት መንገድ ላይም ይመክራሉ ።