loading
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለአረንጓዴ ልማት እንዲነሳ ጥሪ አስተላለፉ::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2012 ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለአረንጓዴ ልማት እንዲነሳ ጥሪ አስተላለፉ:: የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓቢይ አህመድ አሻራችንን በማኖር ለኢትዮጵያ አረንጓዴ ምንጣፍ እንዘርጋ በማለት ጥሪ አቀረቡ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጾቻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የአረንጓዴ ልማት ጥቅም በመረዳት መሥራት ያስፈልጋል። አረንጓዴ ዐሻራ ከሥነ ውበት በላይ ነው። የምንተነፍሰው አየር ነው። የምንጠቀመው እንጨት ነው፡፡ በተፋሰስ በኩል ለግብርና ሥራዎች  የሚደርስ የውኃ አቅርቦት ነው ሲሉ ጽፈዋል። አረንጓዴ ዐሻራ የብዝኃ ሕይወት መመጣጠንን እንደሚፈጥርና  የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑንም አስረድተዋል። የተፈጥሮ ቱሪዝም መስህብን ያሻሽላል። የአፈር መሸርሸርን ይከላከላል። በማለትም ዶክተር ዓቢይ ልማቱ የሚያስገኘውን ጥቅም አብራርተዋል። በኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ የደን  ልማት ለማካሄድ ካለፈው ሣምንት ጀምሮ የአምስት
ቢሊዮን ችግኞች ተከላ ተጀምሯል። ባለፈው ዓመት አራት ቢሊዮን ችግኞች የተተከሉበት እንቅስቃሴ የተደረገ ሲሆን፤ከተተከሉት ችግኞች 84 በመቶ የሚሆኑት መጽደቃቸውን ግብርና ሚኒስቴር  አስታውቋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *