loading
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከአዲስ አበባ ዙሪያ የተፈናቀሉ ዜጎችን እየጎበኙ ነው

አርትስ 08/01/2010
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ቀትር ላይ በአዲስ አበባ በጉለሌ ክፍለ ከተማ መድኃኒአለም ትምህርት ቤት ተገኝተው በአዲስ አበባ ዙሪያ ከተፈናቀሉ ዜጎች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ቡራዩ አቅንተውም በተመሳሳይ መልኩ በመጠለያ ውስጥ ካሉ ዜጎች ጋር ተመሳሳይ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተፈናቃዮችና ተጎጂዎች የሚያነሷቸውን ጥያቄዎችና የችግሩን ስፋት ለማጤን ነው በአካል ተገኝተው ጉብኝት እያደረጉ ያሉት፡፡
በበጎ ፈቃደኞችና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለተፈናቃዮቹ እየተደረገ ያለውን ድጋፍንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተመልክተዋል፡፡
በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ አካባቢዎች በተደራጁ ኃይሎች በርካታ ዜጎች ለሞት፣ ለጉዳት፣ ለንብረት ውድመትና መፈናቀል መዳረጋቸው ይታወሳል፡፡
ችግሩን የፈጠሩ ቡድኖችን በቁጥጥር ስር እያዋለ መሆኑንም መንግስት መግለፁ ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *