loading
ፈረንሳይ በምስራቃዊ ሜዲትራንያን አካባቢ ወታደራዊ ሀይሏን ለማጠናከር እያሰበች ነው ተባለ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ7፣ 2012 ፈረንሳይ በምስራቃዊ ሜዲትራንያን አካባቢ ወታደራዊ ሀይሏን ለማጠናከር እያሰበች ነው ተባለ:: ፓሪስ ሁለት ተዋጊ ጀቶችን ጨምሮ የባህር ሃይል እዝ ወደ ቀጠናው ለመላክ መዘጋጀን ተናግራለች፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው ፈረንሳይ ይህን የምታደርገው ቱርክ ወደስፍራው የጦር መርከቦችን መላኳን ተከትሎ በአንካራ እና በአቴንስ መካከል ውጥረት በመፈጠሩ ነው ተብሏል፡፡

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በአካባው የተፈጠረው ሁኔታ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት እንዳያበላሸው ስጋት ይፈጥራለው ብለዋል፡፡
ማክሮን ሀገራቸው በቀጠናው ወታደራዊ ሀይሏን የምታጠናክረው ሀኔታውን በቅርበት ለመከታተልና ዓለም አቀፍ ህግን ለማስከበር ካላት ቁርጠኝነት ነው ብለዋል፡፡ ቱርክ እና ግሪክ በሜዲተርራንያን ባህር አካባቢ በሚገኝ የሀይድሮ ካርበን የተፈጥሮ ሀብት የይገባኛል ጥያቄ የገቡበት ውዝግብ እየተካረረ መጥቷል ነው የተባለው፡፡ ይህ በተፈጥሮ ጋዝ የበለፀገ የውሃ ክፍል በቱርክ፣ በቆጵሮስ እና በእስራኤል መካከልም ሌላ የውዝግብ ምንጭ መሆኑ ይታወቃል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *