ፑቲንና ትራምፕ ፓሪስ ላይ ተገናኝተው ተወያይተዋል
አርትስ 03/ 03/2011
የዋይት ሀውስና የክሬምሊን ቃል አቀባዮች እንደተናገሩት ፕዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የአሜሪካው አቻቸው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያደረጉት ውይይት ስኬታማ ነበር፡፡
አንድ መቶኛውን የ1ኛው የዓለም ጦርነት ማበቂያ መታሰቢያ በዓል ለመታደም ፈረንሳይ ላይ የተገናኙት ሁለቱ መሪወች በፓሪስ ቤተ መንግስት ምሳ አየበሉ ነው ውይይቱን ያደረጉት፡፡
ሲ ኤን ኤን እንደዘገበው በውይይቱ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና የጀርመኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ተሳታፊወች ነበሩ፡፡
የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ሳራ ሳንደርስ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት መሪወቹ በኒውክሌር፣ በዓለም አቀፍ ንድግድ፣ በሶሪያና በሰሜን ኮሪያ፣ እንዲሁም በሳዲ አረቢያ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡