loading
ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ የአየርላንድ ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጋበዙ፡፡

ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ የአየርላንድ ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጋበዙ፡፡

ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ይህንን ግብዣ ያቀረቡት በትናንትናው ዕለት ከአየርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር  ሊዮ ቫራድካርን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ነዉ ፡፡

በውይይቱ ኢትዮጵያ በተለይ በዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተልዕኮና የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል በመሆን ያከናወነቻቸው ተግባራት በዓለም ደረጃ አድናቆትን እንዳስገኘላት ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዮ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ደረጃ ከፍተኛዋ የአየርላንድ የልማት አጋር መሆኗን በመጥቀስ ይህንን አጠናክሮ ለመቀጥል ሀገራቸው በትብብር ለመስራት ፍላጎት እንዳላትም ጠቁመዋል፡፡

ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ በበኩላቸው አየርላንድ በተለይ በግብርናና በአግሮ ፕሮሰሲንግ እንዲሁም የከብት ልማት ያላት በመሆኑ ኢትዮጵያም በርካታ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመገንባት ላይ ያለች መሆኗን ጠቅሰው በርካታ የአየርላንድ ኢንቨስተሮች ተሳታፊ እንዲሆኑ ጋብዘዋል፡፡

ከፕሬዚደንት ፅ/ቤት ባገኘነው መረጃ ሁሉቱ መሪዎች ስለአየርላንድና አፍሪካ ግንኙነት፣ ስለ ተ .መ.ድ.ና አየርላንድ የጸጥታው ምክር ቤት እጩነትዋ ላይ ተወያይተዋል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *