ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ዩኤንዲፒ ተወካይ ጋር ተወያዩ
አርትስ 19/03/2011
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ከተወካዩ ጋር በነበራቸው ቆይታ በኢትዮጵያ በሚካሄደው የለውጥ ሂደት ላይ መምከራቸው ነው የተሰማው።
ፕሮግራሙ በዚህ የለውጥ ሂደት ላይ አስተዋጽዖ ማበርከት በሚችልባቸው መንገዶች ዙሪያ ጋር መነጋገራቸውም ተገልጿል፡፡
እንደ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት መረጃ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ከተመድ የልማት ፕሮግራም ተወካይ በተጨማሪከሌሎች የስራ ኃላፊዎች ጋርም ተወያይተዋል፡፡
ፕሬዚዳንቷ በቀድሞው የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ፀሐፊ ባንኪሙን እና በኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ከተቋቋመውየአየር ንብረት ኮሚሽን የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ማካሄዳቸውም ተነግሯል።