ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ መሃመት ጋር ተወያዩ
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ መሃመት ጋር ተወያዩ
አርትስ 28/02/2011
የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ መሀመትን ትላንት በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ እና የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ መሀመት በነበራቸው ቆይታም በአፍሪካ ወቅታዊ ጉዳዮችና ምሰራቅ አፍሪካ ሰላምና ፀጥታ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
ከዚህ ባለፈም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ መሀመት ለፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በፕሬዚዳንትነት በመመረጣቸው የተሰማቸውን ደስታ በመልካም መኞታቸው ገለጸውላቸዋል።