loading
ፕሬዚዳንት ኡሁሩ የኬንያ የፓርላማ አባላት የአገልግሎት ክፍያ ጥያቄን አልቀበልም አሉ

ፕሬዚዳንት ኡሁሩ የኬንያ የፓርላማ አባላት የአገልግሎት ክፍያ ጥያቄን አልቀበልም አሉ

አርትስ 28/03/2011

የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሀገሪቱ ፓርላማ አባላት በከፍተኛ ደረጃ ተጠቃሚ ያደርገናል ያሉትን  የአገልግሎት ክፍያ ሪቂቅ አዋጅ ውድቅ አድርገዋል፡፡

የፓርላማ አባላቱ ከራሳቸው ጥቅምና ብልፅግና የበለጠ የህዝቡን ህይወት መለወጥ ላይ ሊያተኩሩ ስለሚገባ የጥቅማጥቅም ጥያቄያቸውን እና የአዋጁን መፅደቅ አልቀበልም ብለዋል ፕሬዝዳንቱ  ፡፡

ሲጂቲኤን አፍሪካ በዘገባው እንዳለው የፓርላማ አባላት የአገልግሎት ክፍያ ከፀደቀ የምክር ቤትና የሴኔት አባላት የመኖሪያ ቤት አበል፣ የተሽከርካሪ ነዳጅ አቅርቦት እና ጥገና እንዲሁም የመኪና ብድር ያገኛሉ፡፡

ይህን የፓርላማ አባላት ጥያቄ  አዋጅ የተቃወሙት ከፍተኛ ባለስልጣናት ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ እና አፈ ጉባዔው ጀስቲን ሙቱሪ ናቸው፡፡

ኬንያውያን ዜጎች   የፓርላማ አባላቱን  የአገልግሎት ክፍያ ጥያቄ በማህበራዊ  ድረ ገፆች እየተቃወሙ ነው ተብሏል።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *