loading
ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የዲሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት የተጀመረው የሪፎርም ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል

አርትስ 30/01/2011

ፕሬዚዳንቱ የፌዴሬሽን እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቶች የጋራ የመክፈቻ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው የበጀት ዓመቱን የመንግስት የትኩረት አቅጣጫዎች ይፋ አድርገዋል::

ክቡር ፕሬዚዳንቱ በመልዕክታቸው የዲሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት የተጀመረው የሪፎርም ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ የዴሞክራሲ ሥርዓቱ እንዲጎለብትና እነዚህ መልካም ጅምሮች በዘላቂነት ተቋማዊ ቅርጽ ይዘው እንዲቀጥሉ በቀጣይነት የሕግ ማዕቀፉን ማሻሻልና የዴሞክራሲ ተቋማትን ማጠናከር ብቸኛው አማራጭ ነው። ይህንን ሂደት በአግባቡ ለመምራት ገለልተኛ የሆነ የሕግና ፍትህ አማካሪ ጉባዔ ተቋቁሟል ብለዋል::

በበጀት አመቱ የጸረ-ሽብር አዋጅ፣ የሲቪክ ማህበራትና የበጎ አድራጎት አዋጅ፣ መገናኛ ብዙሃንና የመረጃ ነጻነት አዋጅ እና ሌሎችን የማሻሻሉ ስራ ይጠናቀቃል።. በተጨማሪም በሚዲያ ነጻነትና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት መከበር ዙሪያ የተጀመረው አበረታች ለውጥ ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን አቶ ፍፁም አረጋ አስታውቀዋል::

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *