loading
ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በአፍሪካ ሀገራት ላይ ጥለውት የነበረውን የጉዞ ክልከላ ማንሳታቸው ተሰማ፡፡

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2014 ባይደን በይፋ እንደተናገሩት የኮቪድ-19 ክትባት የወሰዱ ሰዎች በኦሚክሮን ቫይረስ ቢያዙ እንኳ ለከፋ
ጉዳት እንደማይዳረጉ የህክምና ባለ ሙያዎች አረጋግጠውልኛል ብለዋል፡፡


በመሆኑም በደቡባዊ አፍሪካ ከሚገኙ ስምንት ሀገራት የሚመጡ ተጓዦች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ
ጥለነው የነበረው እገዳ ከእግዲህ አይሰራም ተጓዦቹ መከተባቸው በቂ ነው ብለዋል፡፡
ዋሽንግተን የጉዞ ክልከላ ጥላባቸው የነበሩት ሀገራት ደቡብ አፍሪካ፣ ቦትስዋና፣ ዚምባቡዌ፣ ናሚቢያ፣
ሌሴቶ፣ ኢስዋቲኒ፣ ሞዛምቢክና ማላዊ ናቸው፡፡


ባይደን ለእገዳው መነሳት ያቀረቡት ሌላው ምክንያት የኦሚክሮን ቫይረስ ሀገራችንን ጨምሮ ከ100
በላይ ሀገራት ውስጥ የተሰራጨ በመሆኑ በክልከላው የምናድነው ነገር የለም የሚል ነው፡፡
በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ፈጥነው ስለሚያገግሙ በለይቶ ማቆያ ስፍራ የሚኖራቸውን ቆይታ ከ10 ወደ
5 ቀን ዝቅ ማድረጓንም አሜሪካ አስታውቃለች፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት አዲሱ ቫይረስ በተከሰተ ማግስት የሚደረጉ የጉዞ ክሎከላዎች የኮሮና ቫይረስን
በጋራ የመከላከሉን ጥረት ከማዳከም ውጭ ውጤት እንደማያመጣ አሰጠንቅቆ እንደነበር ይታሰወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *