loading
ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር የሞት ፍርድ የተወሰነባቸዉን ሁለት የፖለቲካ አስረኞች በነፃ ለቀቁ

ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር የሞት ፍርድ የተወሰነባቸዉን ሁለት የፖለቲካ አስረኞች በነፃ ለቀቁ

አርትስ 22/02/2011

የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ከተቀናቃኛቸዉ ሬክ ማቻር ጋር የተደረገዉን ሰላም ለማብሰር ባደረጉት ንግግር ወቅት ነበር የፖለቲካ እስረኞቹ እንዲለቀቁ መወሰናቸውን ይፋ ያደረጉት፡፡

ዘኢስት አፍሪካን እንደዘገበዉ ሳልቫኪር እንዲቀቀቁ የወሰኑላቸው የሬክ ማቻር የቀድሞ ቃል አቀባይ ጀምስ ጋትዴትና የደቡብ አፍሪካ ዜግነት ያላቸዉ ዊሊያም ኤንድሌይ የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው ነበር።

ቃል አቀባይ ጀምስ ጋትዴት በፈረንጆቹ 2017 መንግስትን በመክዳት ወንጀል ነበር ከናይሮቢ ተይዘዉ የታሰሩት፡፡

የደቡብ አፍሪካ መከላከያ ሰራዊት ኮሎኔል የሆኑትና የቀድሞ የሬክ ማቻር አማካሪ ዊሊያም ኤንድሌይ ደግሞ ለሳልቫኪር ተቀናቃኝ ወታደራዊ ድጋፍ አድርገዋል በሚል ክስ ቀርቦባቸው የተፈረደባቸው ሲሆን ዛሬ ረፋድ ላይ ከእስር በነፃ እንዲለቀቁ ተደርጓል ተብሏል፡፡

ሬክ ማቻር በመስከረም 12ቱ ስምምነት መሰረት ከ2 አመት በኋላ በትናንትናዉ እለት ጁባ መግባታቸዉ ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *