loading
ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሀ ከስልጣን ይውረዱ የሚል ግፊት በዝቶባቸዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሀ ከስልጣን ይውረዱ የሚል ግፊት በዝቶባቸዋል፡፡

የቀድሞው የእግር ኳስ ኮከብ እና የአሁኑ የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ጆርጂ ዊሀ የሀገራቸውን ኢኮኖሚ ከውድቀት  መታደግ አልቻሉም በሚል ተቃዋሚዎቻቸው ወይ ባአግባቡ ይምሩ ወይ ስልጣን ይልቀቁ እያሏቸው ነው፡፡

ፕሬዝዳንት ዊሀ ከተቃዋሚዎች ጋር ለመመካከር እቅድ ቢኖራቸውም  ተቃዋሚዎቹ ግን በመጭው ሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ጠርተዋል ነው የተባለው፡፡

አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ፕሬዝዳንት ዊሃ ተቃዋሚዎቹ ለተቃውሞ ጎዳና ከመውጣታቸው በፊት ሀሳባቸውን ለውይይት ቢያቀርቡ መልካም ነው ይህን ማድረግ ካልፈለጉ ግን መብታቸው ነው ብለዋል፡፡

ዊሃ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ የመጀመሪያው ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ መጠራቱን ተከትሎ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በሀገሪቱ አለመረጋጋት እንዳይከሰት ከወዲሁ ስጋታቸውን እየገለፁ መሆኑንም ዘገባው አመላክቷል፡፡

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *