ፖሊስና ብሄራዊ መረጃና ደህንነት በጋራ ባደረጉት አሰሳ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ ገንዘቦችንና ንብረቶችን ያዙ
አርትስ 17/04/11
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለአርትስ ቲቪ እንዳስታወቀው ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋርበመቀናጀት ባደረገው አሰሳ በህገ ወጥ መንገድ በግለሰቦች እጅ የነበሩ የተለያዩ ገንዘቦችን መያዙን አስታውቋል።
ከዚህ በተጨማሪም በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ልዩ ልዩ ንብረቶችን ይዞ በምርመራእያጣራ መሆኑንም ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡
አሰሳው የተካሄደው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ያደረገውን ጥናት መነሻ በማድረግ ሲሆን ተቋማቱ ላለፉት ሁለት ቀናት ባደረጉት በቦሌ ክፍለ ከተማ ባደረጉት ፍተሻ የውጪ ሀገራትን ገንዘብበመመንዘር ህገ-ወጥ ስራ ላይ ከተሰማሩ ግለሰቦች ላይ መጠኑ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ መያዛቸውም በመግለጫው ተብራርቷል።
በአሰሳው ውስጥም ከ80 ሺ በላይ የአሜሪካ ዶላር ፣ ድርሃም፣ የሳውዲ ሪያል፣ የሱዳን ፓውንድ እና ከ271 ሺ በላይ የኢትዮጵያ ብር በኢግዚቢትነት ተይዟል ይላል መግለጫው።
በወንጀሉ የተጠረጠሩ አምስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ምርመራው እየተጣራ መሆኑንም ኮሚሽኑ የላከልን መረጃ ያመለክታል።
ከተያዙት ገንዘቦች በተጨማሪ በህገ ወጥ መንገድ በኮንትሮባንድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችእና በአንድ ስፍራ ብቻ የተገኙ 1023 የውሃ ቆጣሪዎች ተይዘው ህጋዊነታቸውን ለማረጋገጥ የምርመራስራ እየተሰራ መሆኑንም ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡
ኮሚሽኑ ህብረተሰቡ ለፖሊስ ስራ ስኬታማነት እያደረገ ላለው ትብብር ምስጋናውን አቅርቦ ትብብሩተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን አስተላልፏል፡፡