loading
ለህፃናት ሞት መቀነስ ዋና መፍትሄ ጡት ማጥባት ነው ተባለ ፡፡

ይህ የተባለው አለም አቀፍ ጡት የማጥባት ሳምንትን በተመለከተ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ ላይ ነው፡፡
አለም አቀፍ የጡት ማጥባት ሳምንት በኢትዮጲያ ሲከበር ለ10ኛ ጊዜ ሲሆን “ጡት ማጥባት የሕይወት መሰረት ነው” በሚልመሪ ቃል እስከ ነሃሴ 1ቀን 2010 ዓ.ም ይከበራል ፡፡
በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የእናቶች እና ህፃናት ዳይሪክቶሬት የስርአዓተ ምግብ አማካሪ ወ/ሮ በላይነሽ ይፍሩ ህፃናት ከወሊድ በኋላ ለተከታታይ 6 ወራት የእናት ጡት ወተት ብቻ መውሰድ አለባቸው፡፡ የእናት ጡት ወተት ለእድገት አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮች የያዘ በመሆኑ ህፃናቱ ለሚያጋጥሟቸው የጤና እክሎች እና ሞትን በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀንስ ያደርጋል ብለዋል ፡፡
ለጉዳዩ ሽፋን በመስጠት እና ግንዛቤ በማስጨበጥ የበርካታ ህፃናትን ሕይወት ለማትረፍ መገናኛ ብዙሃን ከጎናችን ሊቆሙ ይገባል ነው ያሉት ዳይሬክተሯ፡፡
በሀገራችን እስከ 96 በመቶ እናቶች ጡት የሚያጠቡ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ከወሊድ በኋላ ለተከታታይ 6 ወራት ጡት ብቻ የሚያጠቡት እናቶች ደግሞ 58 በመቶ ናቸው ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *