loading
ማህበረሰቡ በሀሰተኛ መረጃ እንዳይታለል የጠቅላይ ሚሴቴር ፅህፈት ቤት አሳሰበ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2013 ማህበረሰቡ በሀሰተኛ መረጃ እንዳይታለል የጠቅላይ ሚሴቴር ፅህፈት ቤት አሳሰበ፡፡ ጽህፈት ቤቱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው ጽሁፍ የወንጀለኞች ቡድን የሀሰተኛ መረጃ እያሰራጨ መሆኑን ደርሰንበታል ብሏል፡፡ የወንጀለኞች ቡድን አባላቱ ከቀድሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የግል የኢሜይል አድራሻ የተላከ በማስመሰል መረጃ በመጠየቅ እና ሐሰተኛ ምላሽ በመስጠት ላይ መሆናቸውን አውቀናል ነወ ያለው።

በመሆኑም ሁሉም ሰው ሐሰተኛ መረጃ በመሠራጨት ላይ መሆኑን አውቆ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል፡፡ መሆኑም ህብረተሰቡ እንደዚህ ያሉ አጠራጣሪና ጥፋት የሚያስከትሉ እንቅስቃሴዎችን በሚያይበት ወቅት ለሕግ አስከባሪ አካላት እንዲያሳውቅ ጥሪ አቅርቧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *