ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳን ጨምሮ 11 የፖሊስ አመራሮች በዋስ ቢለቀቁ እንደማይቃወም አቃቤ ህግ አስታወቀ
ሰኔ 16ቱ የመስቀል አደባባይ የድጋፍ ሰልፍ ላይ የአመራርነት ክፍተት አሳይተዋል ተብለው ምርምራ እየተካሄደባቸው የሚገኙት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳ በዋስ ቢለቀቁ አቃቤ ህግ እንደማይቃወም ገለጸ፡፡
አቃቤ ህግ ምክትል ኮሚሽነሩን ጨምሮ ሌሎች 11 የፖሊስ አመራሮችም በዋስ ቢለቀቁ እንደማይቃወም አስታውቋል፡፡
የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎትም በጉዳዩ ውሳኔ ለመስጠት ለነገ ቀጠሮ መስጠቱ ተገልጿል፡፡
እንዲሁም ብርሃኑ ጃፋር ቦንብ የወረውሩትን አካላት በመኪና በመሸኘት እና ጥላሁን ጌታቸው ቦምብ በመወርወር የተጠረጠሩት ግለሰቦች ላይ ፍድር ቤቱ የሰባት ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡