loading
በማይናማሯ መሪ ላይ ግፊት እየበዛባቸው ነው፡፡

ሰሞኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣው ሪፖርት በማይናማር በሮሂንጊያ ሙስሊሞች ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ የዘር ማጥፋት ተግባር መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡
አሁን ደግሞ ይህን ሁሉ ግፍ አና በደል እየተመለከቱ ተጎጅዎችን ለማዳን ሙከራ አላደረጉም በማለት የሀገሪቱ መሪ አውንግ ሳን ሱ ኪ ስልጣናቸውን መልቀቅ አለባቸው የሚል ወቀሳ እነተነሳባቸው ነው፡፡
ቢቢሲ እንደዘገበው በተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሀላፊ ዜይድ ራዳ አል ሁሴን ሳን ሱ ኪን አጥብቀው ተችተዋል፡፡
ሰዎችን ለመርዳት ያን የቁም እስር ዘመን ማስታወስ ነበረባቸው ያሉት አል ሁሴን መሪዋን የዲሞክራሲ አብነት እና የሰላም ተሸላሚ ከሚለው ይልቅ ሊነገር የማይችል የሰብዓዊ መብት ጥሰትን የፈጸሙ የሚለው የበለጠ ይገልፃቸዋል በማለት ወቅሰቸዋል፡፡

አርትስ 24/12/2010

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *