በሰሜን ሸዋ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ12 ሰዎች ህይወት አለፈ
አርትስ 12/02/2011
በሰሜን ሸዋ ዞን አንጎለላን ጠራ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 12 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡
የመምሪያው የመንገድ ትራፊክ ጥናትና ትምህርት ስልጠና ባለሙያ ኮማንደር መካሻ ተስፋዬ እንደገለፁት ከደብረ ብርሃን ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ከጭነት መኪና ጋር ተጋጭቶ ነውአደጋው የደረሰው፡፡
በትራፊክ አደጋው የ12 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ አልፏል፡፡ ሌሎች ቀላል እና ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ደግሞ በደብረ ብርሃን ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ነው፡፡ እንደ ኮማንደሩ ገለፃበአምስት ወራት በወረዳው በተከሰተ ሶስት የትራፊክ አደጋ 43 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
አብመድ