በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ብቻ በኣንድ ሳምንት 150 ቤቶችበህገ ወጥ መንገድ የተያዙ ቤቶች ተገኙ።
አርትስ 26/12/2010
በህገወጥ መንገድ የተያዙ የቀበሌ ቤቶች ተለይተው ለችግረኞች ይተላለፋሉ ብለዋል የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ። በህገወጥ መንገድ የተያዙ የቀበሌ ቤቶችን በሁሉም ክፍለ ከተማ የማጥራት ዘመቻ ቀጥሏል ሲል የከንቲባ ፅ/ ቤት አስታውቋል።
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ብቻ በአንድ ሳምንት 150 ቤቶች ተገኝተዋል።ቤቶቹም በዚህ ሳምንት ለተቸገሩ እና አንገት ማስገቢያ ላጡ ነዋሪዎች እንደሚተላለፉ ም/ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ገልፀዋል።