loading
በኢትዮጵያ የአሸናፊዎች አሸናፊ ጨዋታ መከላከያ የዋንጫ ባለቤት ሲሆን በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ዩቬንቱስ፣ ማድሪድና ማንችስተር ሲቲ ድል ቀንቷቸዋል
አርትስ ስፖርት14/02/2011
ትናንት በአዲስ አበባ ስታዲየም 11፡00 ስዓት ላይ በ2010 ዓ/ም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ጅማ አባ ጅፋር እና በኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ አሸናፊ መከላከያ መካከል የአሸናፊዎች አሸናፊ የዋንጫ ጨዋታ ተደርጓል፡፡
በጨዋታው መከላከያ በኤልያስ ማሞ እንዲሁም ጅማ አባ ጅፋር በሳሙኤል ታየ ግብ አስቆጥረው ሁለቱ ቡድኖች ሙሉውን ጨዋታ በአንድ አቻ ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ በተሰጠው የመለያ ፍፁም ቅጣት ምት የጦሩ ቡድን መከላከያ 4 ለ 2 በመርታት ዋንጫውን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሰልጣኝ ስዩም ከበደ እየተመራ ከፍ ማድረግ ችሏል፡፡
………………………….
በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ሶስተኛ ጨዋታዎች ትናንት ምሽት መከናወን የጀመሩ ሲሆን ከምድብ አምስት እሰከ ሰምንት የሚገኙ ቡድኖች ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡
በዚህም በምድብ አምስት ባየር ሙኒክ ኤኢኬ አቴንስን በማርቲኔዝና ሉዋንዶውስኪ ግቦች 2 ለ 0፤ አያክስ ቤኔፊካን 1 ለ 0 ረትተዋል፡፡
በምድብ ስድስት ማንችስተር ሲቲ በሲልቫ፣ ላፖርቴና በርናረዶ ሲልቫ ግቦች ሻክታር ዶኔስክን 3 ለ 0 ሲያሸንፍ፤ ሆፈንየም ከ ሊዮን 3 ለ 3 ተለያይተዋል፡፡
በምድብ ሰባት ሪያል ማድሪድ ቪክቶሪያ ፕለዘንን በቤንዜማና ማርሴሎ ጎሎች 2 ለ 1 እንዲሁም እዚሁ ምድብ ሮማ ሲ.ኤስ.ኬ.ኤ ሞስኮውን በዤኮ ሁለት ግብ እና ኡንደር 3 ለ 0 ረትተዋል፡፡
በመጨረሻው ምድብ ስምንት ደግሞ በተጠበቀው ጨዋታ ኦልድትራፎርድ ላይ ዩቬንቱስ በፓብሎ ዲባላ ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 አሸንፏል፤ ያንግ ቦይስ ከ ቫሌንሲያ 1 ለ 1 ተለያይተዋል፡፡
ዛሬ ምሽት ምድብ አንድ ላይ ክለብ ብሩዥ ከ ሞናኮ (ምሽት 1፡55)፤ ቦርሲያ ዶርትሙንድ ከ አትሌቲኮ ማድሪድ (ምሽት 4፡00) ይጫወታሉ፡፡
በምድብ ሁለት፡ ፒ.ኤስ.ቪ አይንዶቨን ከ ቶተንሀም (1፡55)፤ ባርሴሎና ከ ኢንተር ሚላን(4፡00) ይገናኛሉ፡፡
በሶስተኛው ምድብ፡ ሊቨርፑል ከ ክሬቪና ዚቨዝዳ እንዲሁም ፒ.ኤስ.ጂ ከ ናፖሊ (በተመሳሳይ ምሽት 4፡00) ይፋለማሉ፡፡
በምድብ አራት ጋላታሳራይ ከ ሻልክ 04 እና ሎኮሞቲቭ ሞስኮ ከ ፖርቶ (4፡00) ይገናኛሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *