
በጅግጅጋ ከተማ የተጎዱ ወገኖችን ለመርዳት የተላከው የጤና ባለሙያዎች ቡድን ትላንት ሀምሳ ዘጠኝ ለሚደርሱ ተጎጂዎች የህክምና እርዳታ አደረገ፡፡
ከታካሚዎች ዉስጥም ሰላሳ የሚሆኑት ቀዶ ጥገና የሚያስፈልጋቸው ናቸው ። ከነዚህ ዉስጥም ዘጠኝ ለሚሆኑ ተጎጂዎች ቀዶ ጥገና የተደረገ ሲሆን የተቀሩት በዛሬ እለት የቀዶ ጥገና ህክምና እርዳታ ይደረግላቸዋል ተብሏል።
የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን ለጤና ባለሙያዎቹ ምስጋና አቅርበዋል፡፡