loading
በ2010 በጀት ዓመት ለመጠጥ ውሃ አቅርቦትና ሳኒቴሽን ፕሮግራም ከመንግሥትና ከአጋር የልማት ድርጅቶች 2.2 ቢሊዮን ብር ስራ ላይ ውሏል ተባለ፡፡
በአገር አቀፍ ደረጃ 68.6 ሚሊዮን ዜጎች የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
የውሃና መስኖ ሚኒስቴር በድረገፁ እንዳስታወቀዉ መንግሥት የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ተደራሽ ማድረግ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ 2010 በጀት ዓመት መጨረሻ ድረስ በገጠር 56.5 ሚሊዮን፣ በከተማ 12.1 ሚሊዮን በአገር አቀፍ ደረጃም 68.6 ሚሊዮን ዜጎች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
በዚህም መሠረት የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ተደራሽነት ሽፋን በገጠር 73.9% በከተማ 60.2% በአገር አቀፍ ደረጃ 71.1% ማድረስ መቻሉን ተገልጿል፡፡
በዚህም ሂደት ውስጥ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ፣ ክልሎችና ወረዳዎች እንዲሁም መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተሳትፎ አድርገዋል፡፡
አርትስ 24/12/2010

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *