loading
የኒውዮርክ ፍርድ ቤት የቀድሞውን የትራምፕን ጠበቃ ጥፋተኛ ብሏቸዋል፡፡

የቀድሞው የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጠበቃ የነበሩት ሚካኤል ኮሆን ጥፋተኛ የተባሉት በ2016ቱ ምርጫ ለቅስቀሳ ከተመደበው ገንዘብ ህጉ ከሚፈቅደው ውጭ ክፍያ እንዲፈጸም አድርገዋል ተብለው ነው፡፡
ኮሆን በበኩላቸው ድርጊቱን መፈጸማቸውን አምነው ነገር ግን ይህን ያደረኩት ፕሬዝዳንቱ አዘውኝ ነው ብለዋል፡፡
ቢቢሲ እንደዘገበው የሚካኤል ኮሆን ጠበቃ ይህ ክፍያ ደንበኛየን ኮሆንን ወንወጀለኛ ካስባለ ለምን ፕሬዝዳንት ትራምፕን አያስጠይቅም ሲሉ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እስካሁን በጉዳዩ ዙሪያ ምንም አይነት አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡
ገንዘቡ ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ለዓመታት የዘለቀ ግንኙነት አላት ለተባለቸው የወሲብ ፊልም ተዋናይት ስቶረሚ ዳንኤልስ ሚስጥር እንዳታወጣ ለአፍ ማዘጊያ የተከፈለ ነው ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *