የኒው ዚላንድ ሙስሊሞችን በጅምላ የጨፈጨፈው ወጣት በዕድሜ ልክ እስራት ተቀጣ::
አዲስ አበባ፣ነሐሴ 21፣ 2012 የኒው ዚላንድ ሙስሊሞችን በጅምላ የጨፈጨፈው ወጣት በዕድሜ ልክ እስራት ተቀጣ:: የነጭ የበላይነትን አብዝቶ የሚያቀነቅነው ብሬንተን ታራንት የተባለው የ29 ዓመት ወጣት የፈፀመውን የግድያ ወንጀል ያለ ምንም መከራከሪያ አምኖ ለፍርድ ቤቱ ቃሉን በመስጠቱ ነው ጥፋተኛ የተባለው፡፡ ይህ አውስትራሊያዊ ወጣት ክሪስት ቸርች በተባለ ስፍራ ለፀሎት በተሰባበሱ ሙስሊሞች ላይ በከፈተው ድንገተኛ ተኩስ 51 ሰዎችን መግደሉን በራሱ ምስክርነት አረጋግጧል፡፡ ታራንት ጥፋተኛ የተባለው በ51 ሰዎች ገግድያና በ40 ሰዎች ላይ የግድያ ሙከራ አድርጓል በሚል በጠቅላላው በ91 ክሶች ነው፡፡
በዚህም የአውስትራሊያ ፍርድ ቤት መዝገቡን መርምሮ ሲያበቃ በሁሉም ክሶች በዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡ በመሆኑም 51 ንፁሃን ሰዎችን ገድሎ በቀሪዎቹ አርባ ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ ያደረሰው ታራንት ህይዎቱ እስኪያልፍ ድረስ በእስር ቤት ያልፋል ማለት ነው፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው በታራንት ላይ የተላለፈው የፍርድ ውሳኔ ተከሳሹ ከዚህ ድርጊቱ ለመታረም ቃል ገብቶ የዕስር ጊዜው እንዲቀንስለት የአመክሮ ጥያቄን አይቀበልም፡፡የአውስታራሊያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ የሆኑት ካሜሮን ማንደር ተከሳሹ የመፀፀት ስሜት ባያሳይ ኖሮ ቅጣቱ በቂ ላይሆን ይቸድል ነበር ብለዋል፡፡