loading
የአለም ባንክ ናይጄሪያ በ2030 በከፍተኛ ድህነት ዉስጥ ከሚገኙ ሃገራት ተርታ ትገባለች አለ

አርትስ 12/02/2011

የአለም ባንክ ትንበያ ሪፖርት እንደሚያመለክተዉ ናይጄሪያ በ2030 ከሰሃራ በታች ከሚገኙ 10 ከፍተኛ ድሀ ሃገራት ዉስጥ እንደምትገባ ይጠቁማል፡፡

ብሪተን ዉድስ ተቋም ድህነትና ብልፅግና በተሰኘዉ የ2018 ሪፖርቱ ቀደም ሲል ህንድ የነበረችበትን የአለማችን ድሃ ህዝብ የሚገኝባት ሀገር ቦታ በናይጄሪያ ይተካል ብሏል፡፡

ሪፖርቱ እንደሚያሳየዉ በደቡብ ኤሲያ ሃገራት ከፍተኛ የድህነት መጠን እየቀነሰ የመጣ ሲሆን ከሰሃራ በታች በሚገኙ ሃገራት ግን እየጨመረ መጥቷል፡፡

ይሁን እንጂ በአዉሮፓዉያኑ አቆጣጠር በ2015 የነበረዉ ከፍተኛ ድህነት መጠን 41 በመቶ የነበረ ሲሆን በ2030 ግን አሃዙ ቀንሶ 17 በመቶ ይሆናል ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *