loading
የአልሲሲ የጂቡቲ ጉብኝትና አጋር የማብዛት ስትራቴጂ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19፣ 2013ፕሬዚዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ ከፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳይ ለመምከር ወደ ጂቡቲ አቅንተዋል፡፡ ኢጂፕት ቱደይ በዘገባው እንዳስነበበው አልሲሲ ጂቡቲን ሲጎበኙ በግብፅ ፕሬዚዳንቶች ታሪክ የመጀመሪያው ሰው ሆነው ተመዝግበዋል፡፡ የግብፅ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ቃል አቀባይ ባሳም ራዲ በሰጡት መግለጫ የአልሲሲ ጉብኝት ዋነኛ ዓላማ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነትነ ማጠናከር ላይ የሚያጠነጥን ነው ብለዋል፡፡

ሁለቱ መሪዎች ግብፅና ጂቡቲ በተለይ በኢኮኖሚ፣በደህንነትና በወታደራዊ መስኮች በትብብር የሚሰሩበትን መደላድል መፍጠር ላይ ያተኮረ ውይይት ያደርጋሉ ነው የተባለው ከዚህ በተጨማሪም በቀጠናዊ የልማት ትስስሮችና የመረጃ ለውውጦች ላይ ትኩረት ሰጥተው እንደሚወያዩም ተነግሯል፡፡ አልሲሲ ወደ ጂቡቲ ከማምራታቸው አስቀድሞ ሁለት የግብፅ ወታደራዊ ጀቶች በጂቡቲ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ለተጠቁ ሰዎች ድጋፍ የሚሆን ምግብና መድሃኒት ጭነው ወደስፍራው መጓዛቸው ተሰምቷል፡፡ አንዳንድ የፖለቲካ ታዛቢዎች እንደሚሉት የአልሲሲ የጂቡቲ ጉዞ በግድቡ ደርድር ዙሪያ በያዙት አቋም የአፍሪካ ሀገራትን ከጎናቸው ለማሰለፍ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ አንዱ አካል ሊሆን ይችላል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *