loading
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ በሶስት የምስራቅ እስያ ሀገራት ጉብኝት ሊያደርጉ ነው::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2013 የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ በሶስት የምስራቅ እስያ ሀገራት ጉብኝት ሊያደርጉ ነው::
ፖምፒዮ ከመጭው ኦክቶበር 4 ጀምሮ ለጉብኝት የመረጧቸው ሀገራት ጃፓን ደቡብ ኮሪያ እና ሞንጎሊያ ናቸው፡፡ በነዚህ ሀገራት ጉብኝታቸውም በዋናነት የሰሜን ኮሪያና የቻይናን ጉዳይ አንስተው ከሀገራቱ ጋር ይመክራሉ ነው የተባለው፡፡

ፖምፒዮ ኦክቶበር 6 ላይ አሜሪካ፣ ጃፓን፣ አውስትራሊያ እና ህንድ በመሰረቱት የአራትዮሽ የፀጥታ ፎረም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ እንደሚሳተፉም ታውቋል፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው በደቡብ ኮሪያው ጉብኝታቸው የሰሜን ኮሪያን ጉዳይ አንስተው ተጀምሮ በተቋረጠው የኮሪያ ልሳነ ምድር የኒውክሌር ድርድር ዙሪያ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በደቡባዊ ቻይና ባህር አካባቢ የአሜሪካና ቻይና የገቡበትን እሰጥ አገባ የተመለከተ
ውይይትም የጉብኝቱ አንዱ አካል ነው ተብሏል፡፡ ፖምፒዮ ወደ እስያ የሚያቀኑት በግሪክ፣ ጣልያንና ክሮሺያ ያሚያደርጉትን የአውሮፓ ጉዟቸውን
ካጠናቀቁ በኋላ ነው፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የአሜሪካ ምርጫ መቃረቡን ተከትሎ በተለያዩ ሀገራት እየተዘዋወሩ ዋሽንግተን ከውጭው ዓለም ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *