loading
የክብርት ዶክተር አበበች ጎበና የቀብር ስነ-ስርዓት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 29፣ 2013 በቀብር ስነ ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ፓትርያሪክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ፣ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳና የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ተገኝተዋል፡፡

አፍሪካዊቷ ማዘር ቴሬዛ በመባል የሚታወቁት ክብርት ዶክተር አበበች ጎበና ከሀገር ባለውለታነት አልፈው ለሰው ልጆች ትልቅ ክብርን በመስጠት በተለያዩ ምክንያቶች ወላጆቻቸውን ላጡ ህጸናት እናትም አባትም ሆነው ሰው ከወደቀበት ቀና እንዲል አድርገዋል። ክቡር የሆነውን የሰውን ልጅ ከጎዳና እያነሱ አጥበው፣ አብልተው፣ አስተምረው በርካታ ልጆችን ለቁም ነገር ማብቃት የቻሉ ጀግና እናት ነበሩ፡፡ የበርካቶች እናት ክብርት ዶክተር አበበች ጎበና በኮሮና ህመም ምክንያት በጳውሎስ ሆስፒታል በጽኑ ህሙማን ክፍል ሲረዱ ቆይተው ሰኔ 27/2013 ዓ.ም ነበር በተወለዱ በ85 ዓመታቸው ህይወታቸው ያለፈው::

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *