loading
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ በሳምንታዊ መግለጫቸው በአበይት ፖለቲካዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊ እና የዜጋ ዲፕሎማሲ ክንውኖችን ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 2፣ 2013  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ በሳምንታዊ መግለጫቸው በአበይት ፖለቲካዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊ እና የዜጋ ዲፕሎማሲ ክንውኖችን ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡

ትናንት በመንግሥታቱ የድርጅት ፀጥታ ምክር ቤት የቀረበው የታላቁ የህዳሴ ግድብ ጉዳይ የሶስትዮሽ ድርድሩ ወደ አፍሪካ ህብረት እንዲመለስ የሚል ሀሳብ መቅረቡ ትልቅ ዲፕሎማሲ ስኬት ነው ብለዋል።

ቋሚ አባላትም ሁሉም በሚባል ደረጃ ወደ አፍሪካ ህብረት እንዲመለስ ድጋፍ በመስጠታቸው ከዚህ በኋላ የአፍሪካ ጉዳይ በአፍሪካ እንዲታይ የሚደረግ ይሆናል ነው ያሉት።
በኒውዮርክ ኢትዮጵያውያን ያሳዩት ሰላማዊ ሰልፍ ትልቅ አዎንታዊ ተጽእኖ ያሳደረና ሁሉንም የሚያስመሰግን ተግባር መሆኑንም አብራርተዋል።

ቀደም ብሎ በናይል ተፋሰስ አገሮች አምባሳደሮች ውይይት መደረጉን ያስታወሱት አምባሳደር ዲና ሱዳን እና ግብፅ ግድቡን የፀጥታ ጉዳይ ለማድረግ የሞከሩበት መንገድ አግባብ እንዳልሆነና ግድቡ የልማት አጀንዳ መሆኑን አምባሳደሮቹ በአጽንኦት መናገራቸውን ገልጸዋል።

የፀጥታው ምክር ቤት ጉዳዩን አይመለከተውም የሚለው የአረብ ሊግ ጥያቄ የአፍሪካ ህብረትን ሚና አሳንሶ የማየት ጉዳይ እንደሆነም አምባሳደሮቹ መናገራቸውን ጠቁመዋል።
በትግራይ የተደረገው የተናጠል ተኩስ አቁም በአዲስ አበባ ለሚገኙ ለውጭ ዲፐሎማቲክ ማህበረሰብ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገለፃ መደረጉንም አንስተዋል።

ለትግራይ ክልል ለሚደረገው የሰብአዊ እርዳታ የአለም አቀፍ ተቋማት የበረራ ፍቃድ ቢሰጥም እያንዳንዱ በረራ አዲስ አበባ ካረፈ በኋላ ወደ ትግራይ እንደሚሄድና ሲመለሱም አዲስ አበባ አርፈው መሄድ ይኖርባቸዋል ብለዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *