loading
የ4ዓመት ከ9ወር ዕድሜ ያላትን ህጻን አግቶ የወሰደዉ ግለሰብ ተያዘ::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 8፣ 2013 የ4ዓመት ከ9ወር ዕድሜ ያላትን ህጻን አግቶ የወሰደዉ ግለሰብ ተያዘ:: የ4ዓመት ከ9ወር ዕድሜ ያላትን ህጻን ከትምህርት ቤት አግቶ በመውሰድ ገንዘብ የጠየቀው ግለሰብ ከአዲስ አበባ ውጪ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንዳስታወቀዉ የእገታ ወንጀሉ የተፈፀመው ሰኔ 29 ቀን 2013 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 10 ሰዓት ተኩል ገደማ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ነው፡፡

ተጠርጣሪው ግለሰብ የህፃኗ ወላጆች ንብረት በሆነ ሆቴል ውስጥ ለ2 ዓመታት ያህል በጥበቃ ሰራተኝነት እያገለገለ የቆየ ሲሆን ፤ በዕለቱም ህፃኗን ከምትማርበት ት/ቤት እንዲያመጣት በወላጆቿ ሲታዘዝ እሱ ግን የታዘዘውን ወደ ጎን በመተው ህፃኗን ይዞ መሰወሩን ፖሊስ ገልጿል፡፡ ግለሰቡ ልጃችሁን አግቻታለሁ 250 ሺህ ብር አዘጋጁ ካለበለዚያ አታገኟትም የሚል ማስፈራሪያ በስልክ ሲያደርሳቸው ለፖሊስ ሪፖርት ማድረጋቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ የክትትልና ኦፕሬሽን ክፍል የህፃኗ መጥፋት ሪፖርት ከደረሰው ሰዓት ጀምሮ ተጠርጣሪውን የማፈላለግ ስራ ሲሰራ ቆይቶ በታገተች በሁለተኛው ቀን ሃምሌ 01 ቀን 2013 ዓ.ምበኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን ፍቼ ከተማ ውስጥ ህፃኗን ይዞ ሲንቀሳቀስ በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ በተጠርጣሪው ላይ ምርመራ እየተጣራ መሆኑንም ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *