loading
ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በጣልያን-አፍሪካ የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ይገኛሉ

አርትስ 14/02/2011

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በጣሊያን አፍርካ የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ለመካፈል ወደ ጣልያን አቅንተዋል።

ጥቅምት 15 እና 16 ለሁለት ቀናት በሚካሄደው በዚሁ ስብሰባ ላይ የሚገኙት ዶክተር ወርቅነህ አንድ ከፍተኛ የልዑካን ቡድንን በመምራት ነው ወደጣሊያን ያቀኑት ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከስብሰባው ጎን ለጎን ከጣልያን ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በመገናኘት በሀገራቱ የጋራ አጀንዳዎች ላይ ይወያያሉ ተብሏል፡፡

መድረኩ የጋራ በሆኑ ዓለምዓቀፋዊ፣ አህጉራዊና ቀጠናዊ የሰላምና ጸጥታ አጀንዳዎች እንዲሁም ፍልሰትን በሚመለከት መኖር በሚገባቸው ትብብሮችና የመፍትሄ ሃሳቦች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚመክርም ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል፡፡

በስብሰባው የጣልያን ፕሬዝዳንት፣ ጠቅላይ ሚንስትርና የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩን ጨምሮ 45 የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስትባለስልጣናት ይገኛሉ ተብሏል፡፡

ስብሰባው ከ350 በላይ ልዑካኖች ይታደሙበታል ተብሎ ይጠበቃል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *