loading
ሱዳን የዩንቨርሲቲ ፕሮፌሰሮችን አሰረች፡፡

ሱዳን የዩንቨርሲቲ ፕሮፌሰሮችን አሰረች፡፡

የፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር የጸጥታ ሰዎች በካርቱም ለስምንተኛ ሳምንት የቀጠለውን ህዝባዊ አመፅ የተቀላቀሉ 14 መምህራንን ማሰራቸው ተሰምቷል፡፡

ሮይተርስ እንደዘገበው በመንግስት እና በግል ሆስፒታሎች የሚሰሩ ሀኪሞችም በካርቱም እና በሌሎች ከተሞች የአልበሽርን አስተዳደር በመቃወም ጎዳና ወጥተዋል፡፡

የሞያ ማህበራት፣ ተማሪዎች፣ አክቲቪስች እና ወጣቶች ከፈረንጆቹ ታህሳስ 19 ጀምሮ ያለማቋረጥ የሚያደርጉት የተቃውሞ ሰልፍ በቋፍ ላይ የሚገኘውን የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ይበልጥ አደጋ ላይ ጥሎታል ነው የተባለው፡፡

ሰልፈኞቹ  አሁንም  ነፀነታችን ይረጋገጥ፣ ፍትህ ይስፈን፣ ግድያና እና  ማሰቃየት ይቁም የሚሉ ፅሁፎችን ይዘው በየቀኑ የአደባባይ ተቃውሟቸውን አላቆሙም፡፡

አልበሽር ደግሞ በስም የማይጠቅሷቸውን የውጭ ሀይሎች በሀገራችው አለመረጋጋት እንዲሰፍን ጣልቃ በመግባት እየሰሩ ነው ሲሉት ወቀሳ ያሰማሉ፡፡

ሱዳን ባለፈው ብጥብጡን ሲዘግቡ የተገኙ ጋዜጠኞችን ስትፈታ መሻሻሎች ሊታዩ ነው ተብሎ በአንዳንዶች ዘንድ ተስፋ ቢደረግም አሁን ደግሞ የዩንቨርሲቲ መምህራንን ማሰሯ ስጋትን ፈጥሯል፡፡

 

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *