በምዕራብ ወለጋ ዞን በነበረው አለመረጋጋት የተዘረፉ የጦር መሣሪያዎችና ንብረቶች መመለሳቸው ተገለፀ
በምዕራብ ወለጋ ዞን በነበረው አለመረጋጋት የተዘረፉ የጦር መሣሪያዎችና ንብረቶች መመለሳቸው ተገለፀ
የምዕራብ ወለጋ ዞን ኮማንድ ፖስት እንዳስታወቀው በምዕራብ ወለጋ ዞን በነበረው አለመረጋጋት የተዘረፉ የጦር መሣሪያዎችና ንብረቶች ተመልሰው በአሁን ወቅት በዞኑ ሁሉም የመንግሥት መዋቅሮችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወደ መደበኛ ሥራቸው ተመልሰዋል ብሏል፡፡
በዞኑ በነበረው የፀጥታ ችግር የተዘረፉ 110 ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች፣ 41 ሽጉጦችና 20 የእጅ ቦምቦች እንዲሁም ሌሎች ንብረቶች መመለሳቸውን የኮማንድ ፖስቱ ጽህፈት ቤት አስተባባሪ አቶ ደጀኔ ገብረ ማርያም ተናግረዋል፡፡
እንዲሁም 326 ኋላ ቀር ጠመንጃዎችና ከ4 ሺህ በላይ ጥይቶች ፣ 50 በርሜል ነዳጅ፣14 የመንግሥትና የግል ተሽከርካሪዎች ፣28 የሞተር ቢስክሌቶችም በተመሳሳይ መመለሳቸውን አቶ ደጀኔ ተናግረዋል፡፡ ዘገባው የኢዜአ ነው፡፡