loading
በናይጄሪያ የኮሌራ ወረርሽኝ ስጋት::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19፣ 2013  በናይጄሪያ የኮሌራ በሽታ መከሰቱን ተከትሎ 20 ሰዎች መሞታቸው ተሰማ በሰሜናዊው የሀገሪቱ ክፍል በተከሰተ የኮሌራ በሽታ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ የ20 ሰዎች ህዎት ሲያልፍ ከ300 በላይ ሰዎች ደግሞ ሆስፒታል ገብተዋል ተብሏል፡፡ ባውቺ በተባለችው ግዛት የተከሰተው የኮሌራ በሽታ በዘጠኝ ወረዳዎች ላይ ከፍተኛ መስፋፋት ማሳየቱን የግዛቷ ጤና ኮሚሽነር ሞሃመድ ሚጎሮ ገልፀዋል፡፡

አፍሪካ ኒውስ እንዘገበው የጤና ኮሚሽነሩ አክለውም በሽታው በፍጥነት እየተስፋፋ መምጣቱን ተከትሎ በግዛቲቱ በሚገኙት 20 ወረዳዎች ያሉ የጤና ተቋማት የአስቸኳይ ምላሽ ሰጭ ቡድኖች በተጠንቀቅ ላይ እንዲሆኑና ዝግጅት እንዲያደረጉና የኮሌራ ለይቶ ማቆያ ስፍራዎችን እንዲያዘጋጁ ትእዛዝ
ተላልፎላቸዋል ብለዋል፡፡

በሽታው ወደተከሰተባቸው አካባቢዎች መድሃኒትቶችና የህክምና ባለሙያዎች የተላኩ ሲሆን የንፁህ ውሃ አቅርቦትና የግል ንፅህና አጠባበቅ ግንዛቤ የማስፋት ስራዎችም እየተሰሩ ነው ተብሏል፡፡ የናይጄሪያ በሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ማእከል ባወጣው ሪፖርት በሀገሪቱ 8 ግዛቶች ከኮሌራ በሽታ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መሆናቸውን ጠቁሟል፡፡ በነዚሁ ግዛቶች ውስጥም ካለፈው ጃኑዋሪ ወር ጀምሮ ከ1 ሺህ 700 በላይ ሰዎች ላይ በሽታው የተገኘ
ሲሆን ከነዚህ መካከል 50 የሚሆኔት መሞታቸው ታውቋል የተባለው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *