በድሬዳዋ ከተማ ከትናንት ጠዋት ጀምሮ በተከሰተው ግጭት የአሥር ሰዎች ህይወት ማለፉን፣ የአካል ጉዳት መድረሱን እና ንብረት መውደሙን ፖሊስስ ገለፀ፡፡
ግጭቱ በተከሰተበት ቀበሌ 09 እና አካባቢው በአሁኑ ሰዓት የተረጋጋ ሁኔታ መኖሩን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ለአርትስ ቲቪ አስታውቋል፡፡
የሰዎች ህይወት ያለፈው ከእሳት ቃጠሎ ጋር በተገናኘ እንደሆነ የገለፀው ፖሊስ ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ የተጠረጠሩ ሰዎችን በቁጥጥር ስር እያዋልኩ ነው ብሏል፡፡
የሰላም ተምሳሌቷ ድሬ ወደቀድሞ ሰላሟ እንድትመለስ ወጣቶችና የአገር ሽማግሌዎች አሁንም እየሰሩ እንደሆነ የገለፁልን ዋና ሳጅን ባንታለም ግርማ የፖሊስ ኮሚሽኑ የህ/ግንኙነት ዲቪዥን ኃላፊ ናቸው፡፡
የተከሰተው ግጭት ብሔርን መሰረት ያደረገ አይደለም ያሉት ኃላፊው መነሻውን ፖሊስ እያጣራ በመሆኑ በቀጣይ ይገለፃል ብለዋል፡፡