loading
የመጀመሪያው የቴክኖሎጂ ከተማ በባህር ዳር ሊገነባ ነው፡፡

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትና ከአሜሪካው ሀብ ሲቲ ላይቭ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በባህር ዳር ከተማ የመጀመሪያውን የቴክኖሎጂ ከተማ (Technology Hub City) ለመገንባት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የምክክር መድረክ አዘጋጅቷል፡፡
የምክክር መድረኩ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ነገ ይካሄዳል፡፡
ምክክሩ Ethiopia is the Real WAKANDA በሚል ርዕስ እንደሚካሄድ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በገፁ ፅፏል፡፡
የቴክኖሎጂ ከተማው በከፍተኛ ወጪ የሚገነባ ሲሆን ወደ ስራ ሲገባ ለቴክኖሎጂ ዘርፉ ከሚያደርገው ድጋፍ በተጨማሪ በኢኮኖሚው ላይ መነቃቃትን ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በገፁ እንዳሰፈረው በመድረኩ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ይሳተፋሉ ብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *