loading
የአሜሪካ ኤምባሲና የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጽ/ቤት ለኢትዮጵያ ቀጠሮ አልያዙም::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19፣ 2013 የአሜሪካ ኤምባሲና የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጽ/ቤት ለኢትዮጵያ ቀጠሮ አልያዙም:: የብሔራዊ ክብር በሕብር አስተባባሪ ኮሚቴ ከብሪታኒያ ኤምባሲ ተወካዮች ጋር ውይይት አደረገ:: ኢትዮጵያ ላይ እየደረሰ ያለውን የውጭ ጣልቃ ገብነትን በመቃወም የተቋቋመው የብሄራዊ ክብር በህብር አስተባባሪ ኮሚቴ በአዲስ አበባ ከሚገኘው የብሪታኒያ ኤምባሲ ተወካዮች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርጓል፡፡

የመርሃ ግብሩ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት በብሪታኒያ ኤምባሲ በነበራቸው ቆይታና የውጭ ጣልቃ ገብነትን በመቃወም እያከናወኗቸው ባሉ ስራዎች ላይ ለመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። ከተለያዩ ታዋቂ ግለሰቦችና አርቲስቶች የተቋቋመው የብሔራዊ ክብር በሕብር አስተባባሪ ኮሚቴ በአዲስ አበባ የብሪ ታኒያ ኤምባሲ በመገኘት ያዘጋጀውን ደብዳቤ መልዕክቱን ለኤምባሲው ተወካዮች አድርሷል። የኮሚቴው አባላት ደብዳቤውን ከማድረስ በተጨማሪ ከኤምባሲው የፖለቲካ አታሼ (ባለሙያና) እና ቆንሱል ጋር በወ ቅታዊ ጉዳዮች ውይይት አድርገዋል። የአስተባባሪ ኮሚቴ አባል አቶ አቢይ ታደለ፤ ግንቦት 13 ቀን 2013 ዓ.ም ለኤምባሲዎች ሊደርስ የነበረው ደብዳቤ ኤ ምባሲዎች ዝግ በመሆናቸው ምክንያት በዕለቱ ደብዳቤን ማስገባት አለመቻሉን ገልጸዋል።

ኤምባሲዎቹ ቀጠሮ በሚሰጡ ጊዜ ደብዳቤን ለማስገባት እቅድ ተይዞ እንደነበረና የብሪታኒያ ኤምባሲ ዛሬ ረፋድ ላይ በሰ ጠው ቀጠሮ መልዕክቱ እንደደረሳቸውና ከኤምባሲው ተወካዮች ጋር ውይይት መደረጉን ገልጸዋል።በደብዳቤው ላይ የውጭ አገራት የኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና የሕዝቦች እኩልነት ማክበር እንደሚገባቸው፣ ከተሳሳተ መረጃ  እንዲርቁ፣ ኢትዮጵያ የጀመረችውን የለውጥ ጉዞ በግልጽ እንዲረዱ መገለጹን ተናግረዋል።

ከብሪታኒያ ኤምባሲ በተጨማሪ ለአሜሪካ ኤምባሲና በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጽህፈት ቤት  ደብዳቤዎቹን ለማድረስ እቅድ የነበረ ቢሆንም ቀጠሮ ስላልሰጡ መልዕክቱን ማድረስ አለመቻሉን  ለኢዜአ ገልጸዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *