
ግብጽ እስረኞችን በይቅርታ መፍታቷን ቀጥላለች፡፡
የሀገሪቱ ባለስልጣናት እንዳስታወቁት ግብጽ በሳምንት ዉስጥ ለሁለተኛ ግዜ እስረኞችን በይቅረታ ፈታለች፡
ታራሚዎቹ ይቅርታዉን ያገኙት በፕሬዝዳንት አብደልፈታ አልሲሲ በኩል ሲሆን ቁጥራቸዉም 1 ሺህ 188 ይሆናል ሲል ሚድል ኢስት ሞኒተር ነዉ የዘገበዉ፡፡
በይቅርታ ከተለቀቁ እስረኞች መካከል 723ቱ ቅደመ ሁኔታ የተቀመጠላቸዉ መሆኑንም ዘገባዉ አመልክቷል፡፡