loading
የመከላከያ ሀይሉ የፀጥታ ችግር የተፈጠረባቸውን አካባቢዎች ማረጋጋት ጀምሯል፡፡

የመከላከያ ሀይሉ የፀጥታ ችግር የተፈጠረባቸውን አካባቢዎች ማረጋጋት ጀምሯል፡፡
የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሞቱማ መቃሳ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት ከጥቂት ቀናት በፊት በኦሮሚያና ኢትዮ- ሶማሌ ክልል አዋሳኝ እና በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች በተከሰቱ ግጭቶች ንፁሃን ለሞትና ለአካል ጉዳት ተዳርገዋል።
የኤፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር አብይ አህመድም የፌዴራል የፀጥታ ሀይሎች በአካባቢዎቹ ተሰማርተው የማረጋጋት እና አጥፊዎችን ለህግ የማቅረብ ስራ ለመስራት እንዲሰማሩ ትዕዛዝ አስተላልፈዉ ነበር ።ይህንን ትዕዛዝ ተከትሎ የኤፌዴሪ መከላከያ ሀይል ግጭት በተከሰተባቸው አከባቢዎች መሰማራቱን የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሞቱማ መቃሳ ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ ባለፈው ሳምንት በቦረና፣ ሞያሌ፣ ምስራቅ ሀረርጌና በሌሎች አካባቢዎች ከሌላው ጊዜ ለየት ያለ ግጭት እንደተከሰተ ገልፀዋል።
በአካባቢው ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ ግጭቶች የተከሰቱ ቢሆንም የሰሞኑ ግጭት ግን ሰፊ አካባቢዎች የሸፈነ እና የበርካታ ዜጎች ህይወት ያለፈበት ነው ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *