loading
የዘንድሮ የሃጂ ጉዞ ዋጋ ላይ ቅናሽ ተደረገ፡፡

የዘንድሮ የሃጂ ጉዞ ዋጋ ላይ ቅናሽ ተደረገ፡፡

ከ15 ቀን በኋላ ለሚደረገዉ ጉዞ 98 ሺህ ብር ይከፈል የነበረ ሲሆን ፤አሁን በተደረገዉ የዋጋ ማስተካከያ ክፍያዉ ወደ 93 ሺህ ብር ዝቅ እንዲል ተደርጓል ፡፡

ከኢትዮጵያ አስልምና ጉዳዮች ጠ/ምክር ቤት የሀጂና ኡምራ ዘርፍ ሀላፊ ሸህ አህመድ የሱፍና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የንግድ ክፍል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ቡሴራ አወል ጉዞዉን በተመለከተ ዛሬ በሰጡት የጋራ መግለጫ ፤አየርመንገዱና ጠቅላይ ምክርቤቱ በጋራ በመሆን ከዚህ በፊት ለትኬት ኤጀንት ይወጣ የነበረዉን ኮሚሽን በማስቀረት በቀጥታ በመስራታቸዉ የዋጋ ቅናሽ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ማስተካከያ እስከተደረገበት አስከዛሬ ድረስ ተጓዦች 98 ሺ ብር የከፈሉ ሲሆን ፤በማስተካከያዉ መሰረት ገንዘባቸዉ ተመላሽ ደረጋል ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *