loading
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ የነበሩት ዶክተር አንዱዓለም አድማሴ ከሀላፊነት ተነሱ።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ የነበሩት ዶክተር አንዱዓለም አድማሴ ከሀላፊነት ተነሱ።

በኩባንያው ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የስራ ሀላፊ ዶክተር አንዱዓለም ከሀላፊነት መነሳታቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አረጋግጠዋል፡፡

በአጠቃላይ በርከት የሚሉ በተለያዩ የስራ ሀላፊነት ላይ የሚገኙ ሰዎች ከሀላፊነታቸው መነሳታቸውን ነው የተነገረዉ።
በዶክተር አንዱዓለም አድማሴ ምትክ ስለተመደቡት የስራ ሀላፊ መረጃ የለም።

ዶክተር አንዱዓለም ከአምስት ዓመት በላይ ኢትዮ ቴሌኮምን በዋና ስራ አስፈፃሚነት አገልግለዋል።

ከሁለት ዓመት ለሚበልጥ ጊዜ በኩባንያው ውስጥ የውስጥ ኦዲተር ዋና ሀላፊ በመሆን ሰርተዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *