loading
ሺ ጂፒንግ ደቡብ አፍሪካ ገብተዋል

የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂፒንግ ለብሪክስ ስብሰባ ነው ደቡብ አፍሪካ የተገኙት፡፡
ፕሬዝዳንቱ በመካከለኛው ምስራቅና በሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች ጉብኝታቸውን የጀመሩ ሲሆን ከነገ ጀምሮ እስከ ዓርብ ድረስ በሚካሄደው 10ኛው የብሪክስ ጉባዔ ይሳተፋሉ፡፡
ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ቻይናና ደቡብ አፍሪካ በጋራ ያቋቋሙት የትብብር ተቋም በዋናነት በሀገራቱ መካከል ያሉትን ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት ታስቦ ነው የተመሰረተው፡፡
ፕሬዝዳንት ሺ ጆሀንስበርግ በምታስተናግደው በዚህ ጉባዔ ከብሪክስና ከብሪክስ ውጭ ካሉ ሀገራት መሪዎች ጋር በጋራ ጉዳዮቻቸው ዙሪያ እንደሚወያዩና መልካም የንግድ ግንኙነቶችን ለመፍጠር ጥሩ አጋጣሚ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ዘገባው የሲጂቲኤን ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *