loading
ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስና ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዮስ ቀጣይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ፓትሪያሪክ ማን ይሆናል?

ይህ ጥያቄ ከእርቁ በኋላ የሚመለስ ቢሆንም ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ግን ለቢቢሲ አማርኛዉ እንደተናገሩት ከሁለቱ ፓትርያሪኮች መካከል የስልጣን መንበሩ ላይ መቀመጥ ያለበት የሚለው ጥያቄ ማነቆ ሆኖ የቆየ ቢሆንም እርሱን አሁን መፍታት ብዙም አይገድም ብለዋል።

ብፁዕ አቡነ ማቲያስ የአስተዳደሩን ስራ እየሰሩ፤ አቡነ መርቆሪዮስን ደግሞ በመንበራቸው ሆነው ከአስተዳደሩ ስራ ግን ገለል እንዲሉ ስማቸውም በቅዳሴ እየተጠራ በሲኖዶሱም እየተገኙ እንዲቀጥሉ ማድረግ አማራጭ ሆኖ እንደሚታያቸው ይናገራሉ።
“አቡነ መርቆሪዮስን የአስተዳደር ስራ ላይ እንዲሳተፉ ቢደረግ ከጤናም ከዕድሜም፣ከአገሪቱ ከሃያ ዓመት በላይ ርቀው ከመቆየታቸውም አንፃር ሊቸገሩ ይችላሉ” ይላሉ።
ቀሲስ ኤፍሬምም በሰጡት ሀሳብ በውጭ አገር ያሉት ፓትርያርክ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም አባቶችና ካህናት ወደ አገር ቤት ተመልሰው በየሀገረ ስብከቱ እንዲመደቡና የአገልግሎት መዋሃድ እንደሚፈጠር ይጠብቃሉ፡፡
ከዚህም ባለፈ ተመሳሳይ ክፍፍል እንዳይፈጠር “ህጎች ይወጣሉ፣መመሪያዎች ይወጣሉ፤ በተለይ ከመንግሥት ጋር ያለው ግንኙነት ምን ዓይነት መሆን እንዳለበት ቤተ ክርስትያን ህግ ታወጣለች ብለን ተስፋ እናደርጋለን።” ብለዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *