loading
መሰረታዊ የንግድ ሸቀጦች ን የምትደብቁ ተጠንቀቁ ተብላችኋል፡፡

መሰረታዊ የንግድ ሸቀጦች ን የምትደብቁ ተጠንቀቁ ተብላችኋል፡፡
ይህንን ያላችሁ የኢፌድሪ የንግድ ሚኒስቴር ነዉ፡፡

ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በላከልን መግለጫ ስንዴ ፣ስኳርና ፓልም ዘይት በመንግስት ድጎማ ወደሀገር ዉስጥ እየገባ ቢሆንም ፤ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ ባደረገዉ አሰሳና በህዝብ ጥቆማ መሰረታዊ ሸቀጦቹ እየተደበቁ እንደሆነ ደርሼበታለሁ ብሏል፡፡
ሚኒስቴሩም መሰረታዊ ሸቀጦች ላይ ህገወጥ ድርጊቶችን የምትፈጽሙ አካላት ከድርጊታችሁ ተቆጠቡ ካልሆነ የሸማቹን መብት ለማስጠበቅ እርምጃ ለመዉሰድ እንደሚገደድ አስታዉቋል፡፡
ህብረተሰቡም መሰረታዊ ሸቀጦች በህጋዊ መንገድ እንዳይሰራጭ የሚያደርጉ አካላትን ሲያይ በነጻ የስልክ መስመር 8478 እና 6319 ደዉሎ ቢያሳዉቀኝ እርምጃ እወስዳለሁ ብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *