loading
አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳ ከዳሸን ቢራ ቦርድ አባልነት ተሰናበቱ

የዳሸን ቢራ ፋብሪካ የቦርድ አባል የነበሩት አቶ በረከት ስምኦን፣ አቶ ታደሰ ካሳና አቶ ወንድወሰን ከበደ ከቦርድ አባልነት መሰናበታቸውን ዳሽን ቢራ አክሲዮን ማህበር ለአርትስ ቲቪ በላከዉ መግለጫ አረጋግጧል፡፡
መግለጫው ተሰናባቾቹን የቦርድ አባላት የተኩት አዳዲሶቹ አባላትን አሳዉቋል፡፡ አባላቱም የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ አህመድ አብተው፣ በቅርቡ የብሔራዊ ባንክ ገዥ የሆኑት ዶክተር ይናገር ደሴ እና የጥረት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር አምላኩ አስረስ ናቸው፡፡
አቶ በረከት ስምኦን፣ አቶ ታደሰ ካሳና አቶ ወንድወሰን ከበደ ከስድስት ዓመታት የቦርድ አባልነት ቆይታ በኋላ መሰናበታቸው ተገልጿል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *